መንግስታዊው ሌብነት ወዴት ይወስደናል ?

በፋሽስቱ ሞሶሎኒ አመራር ሀገራችን ዳግመኛ በጣሊያን መወረሯን ተከትሎ ሀገራችንን ለመርዳት ወደ ሀገራችን በመምጣት በጦርነቱ ላይ በግንባር ተሳታፊ ከነበሩት መሀል ቼክሪፐብሊካዊው የጦር መሀንዲስ አንዱ ነበር፣ ይህ ቼክ ሪፐብሊካዊ ስለ ጦርነቱ የፃፈው እና የሀበሻ ጀብዱ በሚል ወደ አማርኛ የተተረጎመው መፅሀፍ ላይ ስለ ሀገራችን ህዝብ እንግዳ አክባሪነት እና መተሳሰብ እንዲህ በማለት ነበር የተናገረው” ጦርነቱ በተፋፋማበት ወቅት ወራሪው ጣሊያን ከሰማይ የሚያዘንበው መርዛማ ቦንብ እና ከምድር ከሚለቀው ጥይት እኩል አስጊ የሆነው የያዝነው ምግብ በማለቁ የተነሳ የተፈጠረው የረሀብ ስሜት ቢሆንም እንኳ ኢትዮጲያውያኖቹ ምግብ ከየትም ብለው እያመጡ ከራሳቸው በፊት እኛን መመገባቸው ዘለአለም ከህይወቴ የማይጠፋ ከመሆኑም በላይ ስለ ሰው ልጅ አዲስ ነገር ከኢትዮጲያውያኑ እንዳገኝ የረዳኝ ነው ’’ በመፅሀፉ ላይ ጀግኖቹ ኢትዮጲያኖች ለዚህ ቼክአዊ እና ለጉአደኛው የጣልያንን ምሽግ እየሰበሩ ሲጋራ እና መጠጦች ማምጣታቸውን ከዚህ መፅሀፍ ስናነብ አባቶቻችን የሀገራቸውን ሀብት ከዝርፊያ ለማዳን የሚከፍሉት መስዋትነት አስከሞት ለመሆኑ ሊረዳቸው ለመጣው ለእንግዳው ያላቸው እሳቤ እና ክብር እከሞት መሆኑ ማሳያ ነው፡፡

ተቆጥሮ ከማያልቀው የአባቶቻችን ታሪክ ከላይ ኢትዮጲያዊ የሆነውን የሀገር ሀብትን ከዝርፊያ ማዳንን እና መተሳሰብን ያሳያል ብዬ የጠቀስኩትን ታሪክ ሳነሳ ምክንያቴ የተንሸዋረረው የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የእየእለት ተእለት ኑሮአችነን ሲኦል በማድረጉ የተነሳ ኢትዮጲያዊ የሆነውን ሀገር ወዳድነታችንን፣ መተሳሰብአችነን እና መከባበራቸችነን እየተፈተታነው ስለመሆኑ በአንፃራዊነት ለማሳየት ይረዳል ብዬ ነው፡፡ በአለም ላይ የሚገኘው የማይተካውም ሆነ የሚተካው ምድራዊው ሀብት ውስን መሆኑ እነዲሁም የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ የሌለው መሆኑ የሰው ልጅ እነዚህን ሀብቶች በተመለከተ ለሚያደርገው ፉክክር፣ ከፉክክሩ ጋር ተያይዞ ለሚነሳው ግጭት እና ግለኝነት መንስኤ ሆኑአል፡፡ እዚህ ጋር ምድር ላይ ካለው የሀብት እጥረት የተነሳ የሰው ልጅ ሀብቶቹን በማስተዳደር በአስተማማኝ መልኩ መጠቀምን እና በሀብቶቹ አናሳነት የተነሳ በሚፈጠረው ህብረተሰባዊ ፉክክር ወይም ግለኝነትን በተመለከተ የአካባቢ ኢኮኖሚስት(environmental economist) የሆነውን የ ጋሬት ሀርዲን እና የጆሴፍ ሹምፕሰርን ንድፈ ሀሳብ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡

የአካባቢ ኢኮኖሚስት የሆነው ጋሬት ሀርዲን tragedy of the common በሚለው ተደናቂው ስራው ምድር ላይ የሚገኙትን ውስን የሆኑትን በተለይ የማይተኩትን ሀብቶች ኢኮኖሚካል በሆነ መልኩ በመጠቀም ለሚቀጥለው ትውልድ ድርሻውን ለማስተላለፍ ህብረተሰቡ የጋራ የሆኑት ሀብቶቹ ላይ ከመፎካከር መተባበር እንደሚገባው ህብረተሰቡ ውስን በሆኑት ሀብቶች ላይ ከመፎካከር እንዲተባበር ደግሞ የጋራ ሀብቶች ላይ ተቋማዊ የሆነ አስተዳደራዊ ስርአት መዘርጋት ሀብቱን ካለጊዘው እንዳያልቅ እንደሚረዳ ይጠቅሳል፣ ይህ የጋሬት ሀርዲን ንድፈ ሀሳብ ከንድፈ ሀሳብ ባለፈ ነቢር ስለመሆኑ ማሳያው ከሀገራችን ዩኒቨርስቲዎች ከቀዳሚዎቹ አንዱ የሆነው ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ አጠገቡ ተጎልቶ የአለማያ ሀይቅ በህዝቡ፣በድርጅቶች መሀል ባለ የተጠቃሚነት ፉክክር ሊጠፋ የመቻሉ እውነትነት ነው፡፡ ሌላው ውስን ከሆነው የምድራችን ሀብት ጋር በተገናኘ በ እኩሌታ ስለሚኖር ተጠቃሚነት ጆሴፍ ሹምፕሰርን መንግስት የሀገርን ሀብት በውክልና የሚያስተዳድረው መንግስት እንደመሆኑ ተቋማዊ በሆነ አስተዳደር ሀብቱን በእኩሌታ ተጠቃሚ በሚል መርህ በማስተዳደር ለሚቀጥለው ትውልድ የማስተላለፉን ሀላፊነትም ሆነ በፉክክር የተነሳ ለሚደርሰው የሀብት መጥፋት ሀላፊነቱ የመንግስት እንደሆነ democracy, capitalism and socialism በተባለው መፅሀፉ ያትታል፡፡

እነዚህን ከላይ የጠቀስኩአቸውን የ ጋሬት ሀርዲን እና የሹምፕሰርን ንድፈ ሀሳብ መነሻ አድርገን የኢህአዴግ መንግስት የሀገራችንን ሀብት እንደማስተዳደሩ በሀገራችን ሀብት የህዝቡን ኑሮ አሻሻለ ወይ የሚለው ሲመዘን፣ እንደ እኔ እምነት ፖሊሲው የህዝቡን ኑሮ ከማሻሻል ይልቅ የተንሸዋረረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ውጤት የሆነው ሀገራዊው ሙስና እና የጥቅመኝነት ፖለቲካ ሀገራዊውን ሀብት በጥቂት ግለሰቦች እጅ እንዲወድቅ መንስኤ የመሆኑን ሁነት የኢኮኖሚው ፖሊሲ ውጤት ከሆነው የኑሮ ውድነት የብዙሀኑ ህዝቡ ኑሮ ሲኦል እንዲሆን ምክንያት ከመሆኑም በላይ ለኑሮው ሲል ወደ ሀገራዊ ሀብት ዝርፊያ እንዲያመራ መንስኤ ከመሆኑ እንዲሁም የማይተኩት ሀብቶቻችን እንኳን ለሚቀጥለው ትውልድ ሊተላለፉ ለኛም ሳይሆኑ በዘራፊዎቹ ስግብግብነት እየጠፉ ከመሆናቸው ጋር ተገናኝ ስናደርገው ታሪካዊው የሀገራችን ህዝብ የመተሳሰብ እና ሀገር ወዳድነት ባህል ላይ ጥላ እንዳጠላበት እና በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጲያዊ ያልሆነውን አድርባይነት እና ሌበኝነት ብዙሀኑ ህዝብ ከመጤፍ እንዳይቆጥረው የሆነበትን መንስኤ የተንሸዋረረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስለመሆኑ ለማወቅ የሚያስችለን ይመስለኛል ፡፡

በሌላ በኩል የተንሸዋረረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ የፈጠረውን ማህበራዊ ቀውስ ከአለም ኢኮኖሚያዊ ሂደት ጋር ተገናኝ በሆነ መልኩ ማየቱም ቀውሱን ውጪያዊ ነው ወይስ ፖሊሲያዊ (መንግስታዊ) የሚለውን እና ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያያዝ ነው ወይ የሚለውን ለመለየት የሚያስችለን ይመስለኛል፡፡ በዚህ ዘመን ላይ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ ወዘተ በመተሳሰራቸው የተነሳ አለም ወደ አንድ መንደርነት በመቀየሯ የተነሳ ባደጉት ሀገር ካፒታልስታዊው ስርአት የፈጠረው ግለኝነት በፍጥነት በአለም ላይ እንዲዛመት ምክንያት መሆኑን እንዲሁም በኢኮኖሚ እድገት ሂደት ውስጥ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ በሚኖረው ጤናማ ፉክክር የተነሳ ግለኝነት እንደሚፈጠር ባምንም፣ ሌሎች ፖለቲካዊ ሴራዎች እንዳሉ ሆነው እንደእኔ እምነት በሀገራችን በፍጥነት ከመዛመት ባለፈ ባህል ለመሆን የቀረበው ግለኝነት፣ ምን አገባኝነት፣ አለመከባበር፣ሌበኝነት፣ አድርባይነት በአጠቃላይ ኢትዮጲያዊውን መተሳሰብ በግለኝነት እንዲሁም ኢትዮጲያዊ ባህል የሆነው ሀገር ወዳድነት ለሀገር ባለማሰብ የሀገር ሀብትን በመዝረፍ ባህል ለመተካቱ (ሙስና በአሁኑ ጊዜ ከሌብነት ይልቅ እንደ ቢዝነስ የመታየቱን ሀገራዊ ሁነት ልብ ይሉአል) መንስኤው የኢህአዴግ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ፍሬ የሆኑት ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ወንጀል በመባል የሚጠሩት በሀገር ሀብት ፓርቲው መነገዱ ፣ የሀገር ሀብትን ቤተሰባዊ ማድረግ እና ለቤተሰብአዊ ጥቅም ማዋል እንዲሁም የብዙሀኑን ህዝብ ኑሮ ሲኦል ያደረገው የፖሊሲው ውጤት የሆነው የኑሮ ውድነት የፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ ነው፡፡

የቡዝሃኑ ህዝብ እና የሌቦቹ / የሙስኞቹ/ የኑሮ ልዩነት ወዴት ይወስደናል?

ለዚህ ንኡስ ርእስ ሀሳብ መነሻነት እንደመንደርደሪያ የኢኮኖሚ ቀውስ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱን ተከትሎ የሚመጣውን ህዝባዊ ብሶት ከ መንግስታዊ ስርአት ጋር ተገናኝ በሆነ መልኩ ማየቱ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ የስራ አጥ ቁጥር መጨመር፣ ድህነት መጨመር (የቀን ገቢን ከ አንድ ዶላር በታች ለድህነት መለኪያ ቀመርነት በመጠቀም) እና በህብረተሰቡ መሀል የገቢ ልዩነት መስፋት የኢኮኖሚ ቀውስ መገለጫ ናቸው፡፡ በአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ቀውስ ሲከሰት የህዝቡ ብሶት መገለጫው በስርአተ መንግስቱ ባህሪ ላይ የተንጠለጠለ ሲሆን፣ ይህም ማለት ስርአተ መንግስቱ ዲሞክራሲያዊ ከሆነ ህዝቡ በምርጫ ይጥለዋል አልያም ራሱ መንግስቱ በራሱ ፍቃድ ስልጣን ይለቃል፣ ነገር ግን አንባገነንነት የስርአተ መንግስቱ መገለጫ በሆነበት ሀገር የኢኮኖሚ ቀውስ መንስኤው መንግስታዊ ከመሆኑም በላይ የኢኮኖሚ ቀውሱ በህዝቡ ላይ ያደረሰውን መመሰቃቀል ከቁብ ስለማይቆጥረው ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ህዝቡን ኑሮ ሲኦል እንደ ሆነባቸው የሀይቲ ህዝቦች ቤተ መንግስት እስከ መውረር ሊያደርሰው ይችላል እንደ ማለት ነው፡፡

ነባራዊውን የብዙሀኑን የሀገራችንን ህዝብ ኑሮ በተመለከተ አለም አቀፍ ጥናቶችን ከምንም በላይ ደግሞ ተመሳሳዩን ጓዳችንን መነሻ ስናደርግ የኢህአዴግ መንግስት እንደሚለው የኢኮኖሚ ፖሊሲው ፍሬ መገለጫ በተከታታይ ሀገሪቷን በሁለት አሃዝ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳደጉ ሳይሆን የኢኮኖሚ ፖሊሲ መገለጫ ከላይ የጠቀስኩአቸው የኢኮኖሚ ቀውስ ማመላከቻወች ስለመሆናቸው አስረጂ የሚፈልግ አይመስለኝም፡፡ የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መገለጫው በስርአቱ ጥቅመኞች እና በብዙሀኑ መሀል የተፈጠረው የኑሮ ልዩነት እንደመሆኑ፣ ይህ የኑሮ ልዩነት ሀገሪቷን ወዴት ይወስዳታል የሚለውን ለማመላከት እና ለማየት የልማታዊው መንግስት ፖሊሲን ከግንዛቤ በማስገባት የልማታዊው መንግስት ፖሊሲ ፍሬ የሆነውን ሌበኝነት እና ሌበኝነቱ በብዙሀኑ ህዝብ ኑሮ ላይ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ መመሰቃቀል መነሻ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ሀገሪቷን እየመራ ያለው ኢህአዴግ ሀገሪቷን ከድህነት ለማውጣት በሚል የዳቦ ስም የሚያፈሰው ሀገራዊ ሀብት የህዝብን ኑሮ ከማሻሻል ይልቅ ከየትኛውም ዘመን በላይ በሀገሩቷ ላይ መንግስታዊ ሌብነት እንዲስፋፋ እና የጥቂቶች ኑሮ ብቻ እንዲሻሻል መንስኤ ሆኑአል፡፡ ይህ መንግስታዊ ስርአት አልበኝነት የፈጠረው በስርአቱ አገልጋዮች የሚፈፀመው ሀገራዊው ሙስና መንስኤው በልማት ስም የሚፈሰው ሀገራዊ ሀብት እንደመሆኑ እና የሀገሪቷን ሀብት የሚያስተዳድረው ኢህአዴግ ልማታዊ ነኝ ከማለቱ ጋር ስንገምደው በልማት ስም የሚፈሰው ሀገራዊ ሀብት ቀጣይነት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ ሌበኝነቱም ቀጣይነት ስለመኖሩ ማሳያ ነው፡፡ ከሀገር የሚዘረፈው ገንዘብ የኢትዮጲያ ቴሌቪዥን የጉምሩክ እና ገቢዎች ባለስልጣን ሙሰኞች በተያዙ ጊዜ በማስረጃ የተያዘባቸው በማለት እንዳሳየን ስንት እና ስንት ሚሊዮን ብር በጥሬው በቤት ውስጥ፣ በውሃ ማጠራቀሚያ (ሮቶ) ወዘተ መቀመጡ እና አለም አቀፍ ተቋማት የሀገራቸችነን የሙስና ስፋት በተመለከተ የሚያወጡትን ሪፖርት መነሻ ስናደርግ የብዙሀኑ ከላይ እስከ እታች ያለ ቱባ ባለስልጣን በሙስና መነከርን አሳይ ከመሆኑም በላይ በሙሰኞች ላይ የሚደረገው እና የተደረገው ዘመቻ ሀገራዊ ላለመሆኑ አሳይ ከመሆኑ ጋር ተገናኝ ስናደርገው ከተያዘው ውጪ አሁንም በየቤቱ እና በየስርቻው ተዘርፎ የተከማቸው ብር በአንድ በኩል ከባንክ ስርአት ውጪ በመሆኑ የተነሳ በስርአተ ባንክ አማካኝነት በሚዘወረው የሀገሪቷ ኢኮኖሚ ስርአት ላይ የገንዘብ ጉድለት ስለሚያስከትል መንግስትን ለተጨማሪ የብር ህትመት (በዳቦ ስሙ ከብሄራዊ ባንክ መበደር) በመዳረግ ለኑሮ ውድነቱ (ለዋጋ ግሽበት) ቀጣይነት መንስኤ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ዘራፊዎቹ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ሸማች እንደመሆናቸው ነጋዴው በሚያቀርበው ዋጋ የመሸመት አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑ እና ነጋዴው ለሚያቀርበው የተለያዩ ፍጆታዎች፣ አገልግሎቶች ወዘተ የዘራፊዎቹን ፍላጎት (ከትርፉ አኩአያ) ማእከል ማድረጉ የብዙሀኑን ህዝብ ኑሮ በዋጋ ንረት ሲኦል ከማድረጉም በተጨማሪ ፍጆታው የተገደበ እንዲሆን መንስኤ እንደሆነ እና ወደፊትም እንደሚሆን ማሳያ ነው፣ ይህ ሁነት ደግሞ እንደ ሀይቲ ህዝብ ኑሮ ሲኦል የሆነበት ብዙሀኑ ህዝብ ቤተ መንግስቱን ጨምሮ የሌቦቹን ቤት ስለ አለመውረሩ ምንም አይነት ማስተማመኛ እንደሌለ አመላካች ይመስለኛል፡፡

መውጫ

እንግዲህ ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት ኢትዮጲያዊው መተሳሰብ እና ሀገር ወዳድነት የመጥፋት አደጋ መንስኤው የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፍሬ የሆነው ሙስና በሀገር ደረጃ መስፋፋት መሆኑን ከካርል ማርክስ በስርአተ መንግስት ውስጥ ስርአተ አልበኝነት ሲሰፍን ህዝብ ስርአትን ያሰፍናል ከሚለው ህልዬት ጋር ተገናኝ ስናደርገው እንደእኔ እምነት ኢትዮጲያዊ የሆነውን መተሳሰብ እና ሀገር ወዳድነት ከመጥፋት ለመታደግ ብሎም ኑሮአችንን (ጓዳችንን) ከሲኦልነት ለመታደግ፣ ከመዝረፍ፣ ከማዘረፍ ከመራቅ ባለፈ የሚዘረፈው ሀገራዊ ሀብት እዳው ለራስ ብቻ ሳይሆን ገና ወደ ሀገራችን ለሚመጡት (ለሚወለዱት) ጭምር መሆኑን በመገንዘብ ስርአት የማስከበር ሀላፊነትን ስርአቱን ማፈራረስ ድረስ እስከ መሄድ ሀላፊነትን መወጣት የሚገባ ይመስለኛል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: