የማይመግቡን ሰፋፊ የእርሻ መሬቶቻችን

በአሁን ወቅት በአለም ላይ ከ 1.1 ቢሊዮን ህዝብ በላይ ከድህነት ወለል በታች (ከ1 ዶላር በቀን ያነሰ የሚያገኝ) ሲገኝ ከዚህ ውስጥ 74% (810 ሚሊዮን )የሚሆነው ህዝብ ለኑሮ አመቺ ባልሆነ አካባቢ ውስጥ የሚኖር እና በአነስተኛ የግብርና እንቅስቃሴ ላይ ህይወቱን የሚመራ ነው በሌላ በኩል በአላማችን ከ 1960 እኤአ ከ ሶስት ሰው አንዱ በረሀብ የሚሰቃይ የነበረ ሲሆን በ 1990 እኤአ ይህ አሃዝ በመጨመር ከሰባት ሰው አንድ ሆኑአል በተለይ አስደንጋጩ ሁናቴ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ላይ በምግብ እጥረት የሚሰቃየው ሰው በ 2009 እ.ኤ.አ ከ 1 ቢሊዮን ህዝብ በላይ መድረሱ ነው ከዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ ሀገራት የሚገኙ ህዝቦች እንደሆኑ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ተቋም በ2011-,12 ሪፓርቱ ላይ ጠቅሱአል፡፡ እ.ኤአ በ2009 በአለም ላይ ያጋጠመውን የምግብ እህሎች መወደድን ተከትሎ በአለም ላይ ከፍተኛ የምግብ አምራች ሀገራትን በተለይ የሩዝ አምራች የሆኑትን ቻይና እና ህንድን ወደ ውጪ የሚልኩትን ምርት በመቀነስ ቅድሚያ ለሀገር ውስጥ በማለታቸው በነሱ ላይ ጥገኛ ለሆኑት ሀገራት በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከፍተኛ የራስ ምታት ነበር ነገር ግን እነዚህ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በአለማችን ለሚገኙ እውቅ ኢኮኖሚስቶች በከፈሉት ዳጎስ ያለ የፔትሮ ዶላር አማካኝነት በተነደፈ ሀሳብ በአለም ላይ በተለይ በአፍሪካ ለእርሻ ተስማሚ የሆኑ ሀጋራት ውስጥ ለረዥም ጊዜ በሚቆይ የመሬት ኪራይ ለምግብ ፍጆታ የሚውል የግብርና ምርት አምርተው ህዝባቸውን መቀለብ እንዳለባቸው እንዲያምኑ ሆኑአል፡ ይህ ክስተት እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ በአፍሪካ በተለይ ለግብርና ምቹ (ከለምመሬት፣ ለግብርና በቂ የሆነ የመስኖ ውሃ ከመኖር አኩአያ) በሆኑ ሀገራት ከነዚህም ውስጥ በዋነኛነት በተመረጡት ኮንጎ፣ኢትዮጲያ፣ሞዛምቢክ እና ሱዳን ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የመሬት መቀራመት እንዲከሰት ሆኑአል ፡፡ እነዚህ የመካከለኛው ሀራት የሀገራቸውን መልካምድር ለግብርና ምቹ አለመሆኑን በመረዳቸው፣ለርካሽ ጉልበት ሲሉ እንዲሆም ገንዘባቸውን በመተማመናቸው ወደነዚህ ሀገራት ፊታቸውን ማዞራቸው በነዚህ ሀጋርት ውስጥ በሚኖሩ ህዝቦች ላይ ከምግብ ዋስትና አንፃር ጥላውን የሚያጠላ ከመሆኑ እና ከአርሶአደሩ ዋስትና አኩአያ አሉታዊ ጎኑ ስለሚጎላ በሀገራቱ ከሚኖሩ ህዝቦች ከፍተኛ ተቋውሞ እንዲገጥማቸው ሆኑአል ለዚህም ማሳያ የኮሪያው መኪና አምራች ኩባንያ የሆነው ማዝዳ በሞዛምቢክ በገጠመው ጠቃውሞ ለእርሣ የሆሰደውን መሬት ለቄ እንዲወጣ ምክንያት መሆኑ ነው፡፡ ኦክስፋም የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ አለማቀፍ ተቋአም በቂ ምግብ የሚበላባቸው እና የማይበላባቸውን ሀገራት በመለየት የህዝቦችን የረሃብ ደረጃ ለመዳሰስ ባደረገው ጥናት በ125 የአለማችን ሀገራት መረጃ ተንተርሶ በጥር 2006 ባወጣው አለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው የልኬት መስፈርት አማካኝነት ሆላንድን ከአለም ሀገራት አንደኛ በቂ ምግብ የሚገኝባት ሀገር መሆኑአን ሲጠቅስ በመጨረሻ ደረጃ ከምግብ ዋጋ መወደድ የተነሳ እና የምግብ ፍጆታዎችን መግዛት ካለመቻል በቂ ምግብ የማይገኝባት (በቂ ምግብ የማይበላበት) ደግሞ ቻድ ሆናለች ሀገራችን ኢትዮጲያ ቻድን ብቻ በመብለጥ ከመጨረሻዋ ቻድ በላይ ተቀምጣለች፡፡
በሀገራችን ኢትዮጲያ መሬት ለአርሶአዱሩ ከልጁ እኩል የሚያየው ሀብቱ ነው በሌላበኩል ለሀገራችን አርሶ አደር የእርሻ መሬት የማህበራዊም ሆነ የቤተሰባዊ ህይወቱ እሴት መገለጫ ነው፡፡ የመሬት ጉዳይ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ዋጋው ከሌሎች የምድራችን ሀብቶች በተለየ ላቅ ያለ ነው፣ለአፄው ስርወ መንግስት መውደቅ ምክንያት የሆነው የ 1960ው የተማሪዎች አብዮት አብይ አላማው እና መርህው መሬት ለ አራሹ መሆኑ በራሱ መሬት ለማህበረሰብ ምን ያህል ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደአለው ማሳያ ነው፡፡ ህይወቱ በግብርና ላይ ለተመሰረተ አርሶ አደር ለእርሻ መሬቱ ያለው አመለካከት ለምርታማነቱ ወሳኝ አስተዋእፆ አለው በሌላ በኩል መሬት ነክ የሆኑ በፖሊሲ አውጪው የሚነደፉ ፖሊሲዎች በ አርሶአደሩ ምርታማነት ላይ ቀጥተኛ ግኑኝነት ያላቸው ሲሆን የአርሶ አደሩ የግብርና እንቅስቃሴ ደግሞ ከ ሀገራዊ የግብርና ምርታማነት ጋር የተገኛኘ ነው ይህም ማለት የመሬት ፖሊሲውን ጨምሮ ከግብርና እንቅስቃሴው ጋር የሚዛመዱት ላይ ከባለቤትነት ጋር የተገናኙ በፖሊሲ አውጪው የሚነደፉ ፖሊሲዎች የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጨምሮ ከግብርና እንቅስቃሴው ጋር ዝምድና ያላቸውን ነገሮች ባለቤትነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከተው ከሆነ የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚያደበዝዝ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የሰውን ልጅ ተፈጥሮአዊ ባህሪ መነሻ ብናደርግ እንኩአ በራሱ ባለቤትነት የተያዘ ንብረት ላይ ያለ የስራ ተነሳሽነት እና የባለቤትነት ስሜት በሌለው ንብረት ላይ ያለው የስራ ተነሳሽነት ልዩነት እንዳለው መረዳት አዳጋች አይደለም ፡፡ የአንድ አገር የግብርና ምርታማነት መገለጫው የግብርና ምርት የሆኑት የምግብ ፍጆታዎች በገበያው ላይ ባላቸው የአቅርቦት መጠን ሲሆን በገበያው ላይ ያለው የአቅርቦት መጠን ደግሞ የዋጋው መገለጫ ነው በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ የሚገኙ ሀገራት ኢኮኖሚያቸው በኢንደስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ የተገነቡት ሀገራትን ጨምሮ ዋጋን ባማከለ መልኩ ከህዝባቸው የምግብ ዋስትና ቀጣይነት አንፃር ለግብርና ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት እንዲሰጡት ሆኑአል፡፡

የገልፍ ሀገራት ትብብር ( gulf countries cooperation) የተባለው የሳውዲ አረቢያ ድርጅት በ2008 የገልፍ ሀገራት ለምግብ 10 ቢሊዮን ዶላር ማውጣታቸውን በመጥቀስ ይህን በውጪ ሀገራት ላይ የተንጠለጠለውን የምግብ አቅርቦት ለመቅረፍ የአፍሪካ ሀገራትን የዳቦ ቅርጫት ማድረግ እነደሚገባ ይገልፃል ይህንንም ለማሳካት የገልፍ ሀገራት እና የአፍሪካን የትብብር ፎረም ማጠናከር እነደሚገባ ይጠቅሳል፡፡ የ ተቁአሙ የጥናት ክፍል በአፍሪካ ለዚህ ተግባር ሰባት ሀገራት ምቹ እነደሆኑ በመግለፅ በተለየ ሁኔታ ሀገራችን አትዮጲያ ለሀገራቸው የምግብ ፍጆታ ተመራጭ መሆኑአን ይገልፃል፡፡ በዚህ የተነሳ የሳውዲው የግብርና ኩባንያ ጄንታ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ በግብርና ላይ ኢንቨስት ዕያደረገ ሲሆን ሌላኛው የሳውዲ ኩባንያ ሳውዲ ስታር ገሮፐ 2 ቢለዮን ዶላር (ኢንቨስት የተደረገው እና ሊደረግ የታቀደውን ጨምሮ) የሚጠጋ በ1.25 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ኢንቨስት እንዲያረጉ ምክንያት ሁነአል፡፡ በሌላ በኩል በሀገራችን በገጠሩ አካባቢ በፍጥነት የሚጨምረው የህዝብ ቁጥር በሀገራችን ከፍተኛ የግብርና አምራች በሆነው የሀይላንዱ ክፍል ህብረተሰብ ለሚታረስ መሬት እጥረት እየዳረገው ሲሆን እንደ አለም ባንክ ሪፖርት የሚታረስ መሬት በሀገራችን በነፍስ ወከፍ ከ 1960 ከነበረበት 0.7 ሄክታር በ2005 ወደ 0.2 ሄክታር የወረደ ሲሆን ይህ የህዝብ መጨመር እና የሚታስ መሬት እጥረት ደኖችን በመጨፍጨፍ የእርሻ መሬት የማድረግ ውሳኔ በህብረተሰቡ እንዲወሰድ ምክንያት በመሆኑ የአከባቢው ስነምህዳር ላይ ተፅእኖ በመፍጠር ለአካባቢው የዝናብ ቀውስ ምክንያትም ሆኑአል፡፡
የግብርና ምርት ሂደት በባህሪው በተለየ መልኩ ለአደጋ ተጋላጭ ሲሆን በተለይ ባላደጉ ሀገራት መንግስት ለአርሶአደሩ ከሚያደርገው ድጋፍ አናሳነት፣ከግብርና ቴክኖሎጂ አናሳነት፣ዝናብ ላይ ጥገኛ ከመሆኑ የተነሳ ከአየር ፀባይ ለውጥ ጋር በተያያዙ ችግሮች እና ከእርሻ መሬት አናሳነት እና በሌሎች መሰል ፈተናዎች የተነሳ የአርሶ አደሩን የምርት ሂደት በፈተና የተሞላ እና ተስፋ አስቆራጭ ያደርገዋል በዚህም የተነሳ መንግስት ለግብርናው አምራች ሀይል ተግባራዊ የሆነ ልዩ ትኩረት ካላደረገ የግብርናው አምራች ሀይል በከተሞች የኢንደስትሪ እና የኮንስትራክሽን መስፋፋትን ተከትሎ በሚፈጠር የስራ እድል ልቡ እንዲሸፍት ምክንያት ይሆናል ይህ ማለት ደግሞ አምራች የነበረው የሰው ሀይልን ሸማች ከማድረጉ ጋር ተያይዞ ለአጠቃላይ ሀገራዊ የግብርና ምርት መቀነስ ምክንያት ሊሆን ሲችል ማሳያው ደግሞ የግብርና ምርት የዋጋ ንረት (በተለይ በከተሞች እና ከተማ ቀመስ አካባቢዎች) ነው፡፡ በሀገራችን መንግስት የሚጠራው የኢኮኖሚ እድገት አሃዝ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከተው የኢኮኖሚ እድገቱ የግብርና ምርት ዋጋን ሊቀንስ አለመቻሉ ነው፡፡ የግብርና ምርት ዋጋ ቀጣይነት ባለው መልኩ ሊጨምር የሚችለው ገንዘባዊ ( monatery) እና ፍላጎታዊ በሆኑ ምክንያቶች ሲሆን ገንዘባዊ ምክንያት ከመንግስት የገንዘብ ስርአት ጋር በተዛመደ መልኩ በኢኮኖሚው ውስጥ ከኢኮኖሚው አቅም በላይ በሚኖር የገንዘብ መጠን የተነሣ በገንዘብ የመግዛት አቅም ማነስ ጋር የተገናኘ ሲሆን ፍላጎታዊ ምክንያት ደግሞ በከተማ የስራ እድል ከመፈጠር ጋር ተያይዞ አዲስ ሸማች ህብረተሰብ መፈጠር ጋር በተገናኘ እና ከገቢ መጨመር ጋር በተያያዘ መልኩ ከየሚከሰት የፍላጎት መጨመር እና ከአቅርቦት ማነስ ጋር የተገናኘ ነው ዶ/ር ጀማ ሀጂ እና ፍቃዱ ገላው Determinants of the recent soaring food inflation in Ethiopia በተባለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው የሀገራችንን የግብርና ምርት የሆኑት የምግብ ፍጆታዎች የዋጋ ንረት ከገንዘባዊ ምክንያቶች ጋር የተገኛኘ መሆኑን በመጥቀስ የኢኮኖሚ እድገቱ ገንዘባዊ በሆኑ ምክንያት የተነሳ የግብርና ምርቶችን የዋጋ ንረት ሊቀንስ እንዳልቻለ ሲገልፁ በሌላ በኩል አስቴፈን እና አንድሪው የተባሉ አጥኚ Rethinking Agriculture and Growth in Ethiopia በተባለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው የዋጋ ንረቱን የፍላጎትን መጨመር ተያዞ የተከሰተ የአቅርቦት እጥረት መሆኑን በመጥቀስ ከግብርና ምርታማነት ማነስ ጋር የተያያዘ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በዚህ ሁናቴ ውስጥ የሀገራችን መንግስት ይህንን የዋጋ ንረት ለመቀነስ እና ማህበረሰቡን በበቂ ሁኔታ ለመመገብ በፖሊሲ ደረጃ በሰፋፊ የግብርና መሬት የሚካሄድን የግብርና መካናይዜሽን በፖሊሲው ትኩረት አለመስጠቱን ለውጪ ባለሃብቶች የሚሰጣቸው ሰፋፊ ለም መሬቶች ማሳያ ይመስለኛል በሌላ በኩል ደግሞ የውጪ ባለሀብቶች በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ካምፓኒዎች በሀገራችን ለያዙት ግዙፍ ሰፋፊ ለም መሬቶች ምክንያታቸው ለህዝባቸው የምግብ ፍጆታ የሚውል የግብርና ምርት ለማምረት የሚል ነው ይህ ማለት ደግሞ የሀገራቱን የግብርና ምርት ፍላጎት ማሳያ ከመሆኑ አኩአያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ እንኩአን ባይሆን በከፊል ከሚባለው በላይ በራሳችን አምራቾች አምርተን ፍላጎታቸውን በሞምላት የውጪምንዛሬያችንን ለማሳደግ ትኩረት አለመደረጉ እና ተሸላሚ አርሶአደሮቻችን ሚሊዮን ብራቸው ለዚህ ተግባር ካልዋለ (በተበጣጠሰ መሬት ከሚከናወን የግብርና እንቅስቃሴ ወደ መካናይዜሽን የግብርና እንቅስቃሴ ለውጦአቸው የሀገርውስጡን ፍላጎት ማማላት እንደአለ ሆኖ) የግብርና ፖሊሲው ውጤት የተባለው የብራቸው መጠን እና ሀብት ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ እና ትክለኛነቱን የሚያጠራጥር ከመሆኑ ባለፈ የፖሊሲውን አዙሪት የሚያሳይ ሲሆን ሌላው አስደንጋጩ ጉዳይ ደግሞ እንደእኔ እምነት ከረዥም ጊዜ አኩአያ በሀገራችን መሬት የሚያመርቱት የውጪ ባለሀብቶች የግብርና ምርቶቻቸው ወደ ውጪ የምንልከውን የግብርና ምርቶች በአለም ገበያ ላለመፎካከሩ እርግጠኛ አለመሆናችን ነው፡፡

የሀገራችን መንግስት ለውጪ ባለሃብቶች ለተሰጠው መሬት እንደምክንያት የሚጠቅስው የመሰረተ ልማት ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች ባለሃብቶቹ የመሰረተ ልማት ከማስፋፋታቸው አንፃር፣ከቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተለይ ደግሞ የስራ እድል ከመፍጠር አኩአያ ቢሆንም አስቂኙ ነገር በግብርና ላይ ህይወቱን የገነባ ህብረተሰብ በሚበዛበት ሀገር አምራችነቱን በማበረታታት እና ከፖሊሲ አኩአያ ቅድሚያ በመስጠት ለህዝቡ በቂ የሆነ የምግብ ፍጆታ አቅራቢ ከማድረግ ይልቅ በማይመግቡን ሰፋፊ የግብርና ምርት አምራች በሆኑ የእርሻ መሬቶቻችን ላይ እና ለውጪ ሀገር ህዝብ ቀለብ በሚውል የግብርና እርሻ ላይ ተቀጥሮ እንዲሰራ የግብርና የስራ እድል መፍጠሩ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ሁናቴ ውስጥ መንግስታችን የሀገራችን የግብርና ዘርፍ ያለፉትን አስራ አንድ አመታት ጨምሮ በፍጥነት ማደጉን እና እያደገ መሆኑን (ምርት መጨመሩን) ቢገልፅም ትልቁ ጥያቄ ግን መንግስት የግብርናው እድገት ምንጭ የሚለው በ ነፃ እና ገለልተኛ ተቋአማት እና ለሆዳቸው ባላደሩ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሙሁራን ይህንን እድገት የማምጣት አቅሙ ተፈትሾአል ወይ የሚለው እና ከጠቅላላው የሀገሪቱአ የግብርና ሳምፕል ሰርቬይ የሚወሰደው የሰብል ምርት አሃዝ ከአጠቃላዩ የግብርና ሀገራዊ ምርት እድገት አኩአያ ሲታይ ወጥ እና አሳማኝ ነው ወይ የሚለው ይመስለኛል ምክንያቱ ደግሞ በታዋቂው የኦክስፋም አለምአቀፍ ተቀባይነት ባለው የልኬት መስፈርት መሰረት ሀገራችን ኢትዮጲያ በቂ ምግብ ከማይበላባቸው ሀገራት ከመጨረሻዋ ቻድ በላይ መሆኑአ ነው ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: